ለኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረግ

በኤች አይ ቪ መበከልን ለማወቅ የሚቻልበት መንገድ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው ፡፡

scheduleOppdatert: 16.12.2022

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ይህ ምርመራ መደበኛ ሀኪም ተመላላሽ ክሊኒክ ፣ አንዳንድ ድርጅቶች ውስጥ፣ ለወሲብ ጤና ጥንቃቄ እርዳታ የሚሰጥበት ተመላላሽ ሆስፒታል ማለትም     እንደ  ኦላፊያ ተመላላሽ ሆስፒታል (Olafiaklinikken) እና ወሲብ እና ማህበረሰብ (Sex og samfunn)(ከ25 ዓመት በታች ለሆኑ ብቻ ነው) ። ለኤች አይ ቪ ለመበከል ከፍተኛ ለሆነ አደጋ ተጋላጭነት ሁኔታ ሲያጋጥመው አንድ ግለሰብ  የኤች አይ ቪ ምርመራን መውሰድ በነፃ ያለምንም ክፍያ ይሆናል  ፡፡

ሁለት ዓይነት የምርመራ ዘዴዎች  አሉ ፡፡ አንደኛው ተራ የደም ምርመራ ሲሆን  መልስ ለማግኘት በግምት አንድ ሳምንት ይወስዳል። ብዙ ድርጅቶችም ፈጣን የምርመራ መልስ የሚገኝበት የምርመራ ዘዴ አገልግሎትን ይሰጣሉ በደዚህ አይነት ምርመራ የውጤቱ መልስ በደቂቃ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ ፡፡ እነዚህም  ለምሳሌ በጤና አገልግሎት ኮሚቴ (Helseutvalget)እና ደቂቃዊ ምርመራ (Minuttesten) ናቸው ፡፡

 ለኤች አይ ቪ የተለከፉ ለአብዛኞቹ ግለሰቧች በበሽታው በተለከፉ ከ2-6 ሳምንታት በኋላ በምርመራው  ላይ ሊታይ ይችላል ፡፡ ለጥቂት ግለሰቦች ግት ትንሽ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል ።ስለዚህም በበሽታው ለመለከፍ አደጋ ተጋልጠው ከነበረ ከ12 ሳምንታት በኋላ  ምርመራውን ቢወስዱ የተሻል ሁኔታ ነው በማለት እናሳስባለን ።

Les også

schedule14.01.2023

→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

schedule31.12.2021

→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።

በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።